Friday, July 8, 2011

     
with my sister
አትቸኩል፤በዚህ ዓለም ምን የሚያስቸኩል ነገር አለ? ባይቸኩሉም ህይወት ራሷ አጭር ናት፡፡ በዓሉ ግርማ
ስለ ጾታ እኩልነት ምን ታስባላችሁ? እዉነት ሴት ልጅ በወንዶች ይፈፀሙ የነበሩትን ተግባራት (አለባበስ፣የስራ መስክ)ማከናወናቸዉ እኩልነትን ያመጣል? የስራ ክፍፍል ልዩነትስ መኖር የለበትም ወይ? ሴቶች የሚሰሩት ስራ ብዙ ለአደጋ የማያጋልጥ፣ልስልስ ገላቸዉን እና ማህፀናቸዉን የማይጎዳ ስራ ቢሰሩ፤

ሴቶች በተፈጥሯቸዉ በቀላሉ ተሰባሪ ናቸዉ፤በአካልም ሆነ በስነልቦና በቀላሉ ይሰበራሉ፡፡ ስነልቦናዊ ልስላሴያቸዉ ደግሞ ከማህጸናቸዉ ልስላሴ የመጣ ነዉ፡፡ እርስበርስ ካልተፎካከሩ በቀላሉ ይሰበራሉ፡፡ የስነልቦናቸዉ ደረጃ እርስበርስ ከሚደርጉት የፉክክር ዉጤት ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡ወንድ በአካሉ ኤፎካከርም ሴቶች ግን በእያንዳንዱ የሰዉነት ክፍላቸዉ ይፎካከራሉ፡፡ በፉክክሩ ፤ እኩል ወይም የበላይ እንደሆኑ ካልተሰማቸዉ ስነልቦናቸዉ ይጎዳል፡፡
በማህበራዊ ሴሰኝነት ባህል ዉስጥ የመጀመሪያዉ የሴቶች ችግር ስነልቦናዊ ጉዳቱ ነዉ፤ ከዚህ ጉዳትም ለመፈወስ መፍትሄዉ ወሲብ ቀስቃሽ ልብሶችን መልበሰስ ነዉ፡፡
…. ሴቶች ወደ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበሶች ሲሮጡ፤ ወንዶቹ ደግሞ ለልቅ ወሲባዊ ግንኙነት ወደ ሴቶች ይሮጣሉ፤….ማህበራዊ ሴሰኝነት በሴቶች ልቅ የዉበት ስሜት አቀጣጣይነት ህበረተሰቡ ዉስጥ በከፍተኛ ደረጃ የወሲብ ሃይል የመከማቸት ክስተት ነዉ፡፡
ወንድ እና ሴት ሆኖ መፈጠር ለዘመናዊዉ ሰዉ ወይም ስለጡን ነን ባዮች አልተዋጠላቸዉም፡፡ ተፈጥሯዊዉን የፆታ ልዩነት ማበላለጫ እና መሳደቢያ እያደረጉት ነዉ፡፡ ሴት መሆን የመረገም፣ የበታችነት፣ የተጨቋኝነት፣ የደካማነት… ተደርገዉ ተወስደዉ ነበር፡፡  በርግጥ ሴትነት የፍቅር፣ የልስላሴ፣ የርህራሄ፣ የእናትነትና የሰላም ምልክት ነዉ፡፡ ምዕራባዉያኑ (ስሉጥኖች) ሴት እንደ ወንድ ጡንቸኛ፣ ሃይለኛ፣ አመፀኛ እና ጦረኛ እንድትሆን ይፈልጋሉ፡፡
(ፍልስፍና 1፣ብሩህ ዓለምነህ፣አዲስ አበባ፣2003 ከሚል መጽሃፍ የተወሰደ)

Wednesday, July 6, 2011

ሴሰኝነት

የሴሰኝነት ባህሪ ከልቅ የወንዶች ወሲባዊ ፍላጎት ጋር ብቻ ሳይሆን ከልቅ የሴቶች የዉበት ስሜት ጋርም የተገናኘ ነዉ፡፡ ከእንግዲህ አንድ ወንድ ሴሰኛ ነዉ ስንል ልቅ የሆነ የወሲብ ፍላጎት አለዉ፤(ከተለያዩ ሴቶች ጋር በመሆን ጊዜዉን ፣ገንዘቡንእና ሃሳቡን ባብዛኛዉ ለወሲብ ንዳዱ ማስታገሻ ያዉላል ማለታችን ሲሆን)፤ አንዲትን ሴት ሴሰኛ ነች ስንል ደግሞ ልቅ የሆነ የዉበት ፍላጎት አላት፤(ሰዉነቷን የሚገላልጡ እና የሰዉነት ቅርጻን የሚያሳዩ የወሲብ ቀስቃሽ አለባበሶችን የምታዘወትር ከሆነ) ሴሰኛ ናት፡፡      (ፍልስፍና 1፣ብሩህ ዓለምነህ፣አዲስ አበባ፣2003 ከሚል መጽሃፍ የተወሰደ)



….. የዉበት ዋና ዐላማዉ ወሲብን ቀስቅሶ ትዉልድ እነዲቀጥል ማድረግ ነዉ፡፡ ወሲብ ዉበት ላይ ጥገኛ ነዉ፤ ወሲብ (dependent variable) በዉበት (independent variable) ካልተለኮሰ ያንቀላፋል፡፡ የዉበት ዋነኛ ተልኮዉ የወሲብ ስሜትን ማቀጣጠል ስለሆነ፡ ለዉበት ሌላ ሽፋን ልንሰጠዉ አይገባንም፤…. (ፍልስፍና 1፣ብሩህ ዓለምነህ፣አዲስ አበባ፣2003 ከሚል መጽሃፍ የተወሰደ)



የዉበት ተፈጥሯዊ ተልኮዉ ወሲብን መሎኮስ ሆኖ ሳለ፣ የወንዶችን ወሲባዊ ተፈጥሮ አዉገዞ ለሴቶች ልቅዉበት የተለየ መብትእና ሽፋን ለመስጠት የሚደረግ እንቅስቃሴ ያናድደኛል፡፡

(ፍልስፍና 1፣ብሩህ ዓለምነህ፣አዲስ አበባ፣2003 ከሚል መጽሃፍ የተወሰደ)