| with my sister |
አትቸኩል፤በዚህ ዓለም ምን የሚያስቸኩል ነገር አለ? ባይቸኩሉም ህይወት ራሷ አጭር ናት፡፡ በዓሉ ግርማ
ስለ ጾታ እኩልነት ምን ታስባላችሁ? እዉነት ሴት ልጅ በወንዶች ይፈፀሙ የነበሩትን ተግባራት (አለባበስ፣የስራ መስክ)ማከናወናቸዉ እኩልነትን ያመጣል? የስራ ክፍፍል ልዩነትስ መኖር የለበትም ወይ? ሴቶች የሚሰሩት ስራ ብዙ ለአደጋ የማያጋልጥ፣ልስልስ ገላቸዉን እና ማህፀናቸዉን የማይጎዳ ስራ ቢሰሩ፤
ሴቶች በተፈጥሯቸዉ በቀላሉ ተሰባሪ ናቸዉ፤በአካልም ሆነ በስነልቦና በቀላሉ ይሰበራሉ፡፡ ስነልቦናዊ ልስላሴያቸዉ ደግሞ ከማህጸናቸዉ ልስላሴ የመጣ ነዉ፡፡ እርስበርስ ካልተፎካከሩ በቀላሉ ይሰበራሉ፡፡ የስነልቦናቸዉ ደረጃ እርስበርስ ከሚደርጉት የፉክክር ዉጤት ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡ወንድ በአካሉ ኤፎካከርም ሴቶች ግን በእያንዳንዱ የሰዉነት ክፍላቸዉ ይፎካከራሉ፡፡ በፉክክሩ ፤ እኩል ወይም የበላይ እንደሆኑ ካልተሰማቸዉ ስነልቦናቸዉ ይጎዳል፡፡
በማህበራዊ ሴሰኝነት ባህል ዉስጥ የመጀመሪያዉ የሴቶች ችግር ስነልቦናዊ ጉዳቱ ነዉ፤ ከዚህ ጉዳትም ለመፈወስ መፍትሄዉ ወሲብ ቀስቃሽ ልብሶችን መልበሰስ ነዉ፡፡
…. ሴቶች ወደ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበሶች ሲሮጡ፤ ወንዶቹ ደግሞ ለልቅ ወሲባዊ ግንኙነት ወደ ሴቶች ይሮጣሉ፤….ማህበራዊ ሴሰኝነት በሴቶች ልቅ የዉበት ስሜት አቀጣጣይነት ህበረተሰቡ ዉስጥ በከፍተኛ ደረጃ የወሲብ ሃይል የመከማቸት ክስተት ነዉ፡፡
ወንድ እና ሴት ሆኖ መፈጠር ለዘመናዊዉ ሰዉ ወይም ስለጡን ነን ባዮች አልተዋጠላቸዉም፡፡ ተፈጥሯዊዉን የፆታ ልዩነት ማበላለጫ እና መሳደቢያ እያደረጉት ነዉ፡፡ ሴት መሆን የመረገም፣ የበታችነት፣ የተጨቋኝነት፣ የደካማነት… ተደርገዉ ተወስደዉ ነበር፡፡ በርግጥ ሴትነት የፍቅር፣ የልስላሴ፣ የርህራሄ፣ የእናትነትና የሰላም ምልክት ነዉ፡፡ ምዕራባዉያኑ (ስሉጥኖች) ሴት እንደ ወንድ ጡንቸኛ፣ ሃይለኛ፣ አመፀኛ እና ጦረኛ እንድትሆን ይፈልጋሉ፡፡
(ፍልስፍና 1፣ብሩህ ዓለምነህ፣አዲስ አበባ፣2003 ከሚል መጽሃፍ የተወሰደ)